ትዳር እልፍ ምሥጢራትና ውበቶችን የያዘ ድንቅ ግምጃ ቤት ቢሆንም፣ በዘመናችን ብዙ ጥንዶች የዚህን ግምጃ ቤት በሮች ለመክፈት ስንታገልና የሚገጥመንን ግራ መጋባትና የዝምታ ጦርነት ለመፍታት የተሳሳተ ቁልፍ ስንጠቀም ይስተዋላል። ይህ መጽሐፍ የጠፉብንንና የረሳናቸውን የጥበብ መክፈቻዎች ዳግም በእጃችን ላይ ያስቀምጣል።
“መራኁት” የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ቁልፎች፣ መክፈቻዎች” ማለት ነው። እያንዳንዱ ክፍል የተለየ መክፈቻ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ትዳርም በአንድ ቁልፍ ብቻ የሚከፈት ሳይሆን የተለያዩ የጥበብ ቁልፎችን የሚሻ የቅድስና ሕይወት ነው። ይህ መጽሐፍ መንፈሳዊውን ጥበብ ከዘመናዊው የሥነ-ልቡና እና የግንኙነት ሳይንስ (Marriage and Relationship Psychology) እንዲሁም ከሀገርኛ ማኅበራዊ ዕሤቶች ጋር በማዋሐድ፣ ለባለትዳር ጥንዶች መመሪያ፣ ለተደናቀፉ ትዳሮች መፍትሔ፣ ላላገቡ ወጣቶች ደግሞ የቅድመ-ጋብቻ መንገድ መሪ ሆኖ እንዲያገለግል የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው።
ይህ መጽሐፍ ከማይነጥፈው ሥነ-መለኮታዊ የሊቃውንት አስተምህሮ እንዲሁም ከሰፊው የሥነ-ልቡና ሳይንስ ባሕር ላይ ተጨልፎ የቀረበ አንድ ጠብታ ነው!
የጸሐፊው አድራሻ
መጋቤ ጥበብ ይግዛው መኰንን
+251 911 382 753/ +251 983 979 599
[email protected]